Thursday, March 22, 2012

የቦሌ ነገር


የቦሌ ሴትዬ፤ ቦሌ መድኃኔአለም ሄደችና፤ በቦሌኛ ስዕለት መሳል ጀመረች፡፡

‹‹መድዬ! ከውጭ የማስገባቸውን ሀያ ገልባጭ መኪናዎች፤ ቶሎ ካደረስክልኝ፤ በሪሞት ኮንትሮል የሚሰራ ጃንጥላ አስገባለሁ፤ ዕጣንም፤ ጧፍም፤ እ…›› እያለች ሳለ፤ 

ቦሌ መድኃኔአለም እግር የጣላት ደሃ ደግሞ ከጎኗ ተንበርክካ ፈጣሪዋን ‹‹ቸሩ መድኃኒአለም፤ የዕለት እንጀራዬን አትንሳች፤ ጉልበቴን ባርክልኝ፤ ወዘተ…›› እያለች ስትለምን ሰማቻት፡፡
የቦሌዋ ሴትዬ ታዲያ ከቦርሳዋ አስር ብር አወጣችና ‹‹በይ ይህችን ብር ያዥና ሂጂ፤ አጉል መስመር አታጨናንቂ›› አለቻት፡፡

No comments:

Post a Comment