Thursday, March 22, 2012

የቦሌ ነገር


የቦሌ ሴትዬ፤ ቦሌ መድኃኔአለም ሄደችና፤ በቦሌኛ ስዕለት መሳል ጀመረች፡፡

‹‹መድዬ! ከውጭ የማስገባቸውን ሀያ ገልባጭ መኪናዎች፤ ቶሎ ካደረስክልኝ፤ በሪሞት ኮንትሮል የሚሰራ ጃንጥላ አስገባለሁ፤ ዕጣንም፤ ጧፍም፤ እ…›› እያለች ሳለ፤ 

ቦሌ መድኃኔአለም እግር የጣላት ደሃ ደግሞ ከጎኗ ተንበርክካ ፈጣሪዋን ‹‹ቸሩ መድኃኒአለም፤ የዕለት እንጀራዬን አትንሳች፤ ጉልበቴን ባርክልኝ፤ ወዘተ…›› እያለች ስትለምን ሰማቻት፡፡
የቦሌዋ ሴትዬ ታዲያ ከቦርሳዋ አስር ብር አወጣችና ‹‹በይ ይህችን ብር ያዥና ሂጂ፤ አጉል መስመር አታጨናንቂ›› አለቻት፡፡

Tuesday, March 20, 2012

የሽማግሌዎች ጨዋታ

 ሁለት የተወሰነ የእድሜ ልዩነት ያላቸው ሽማግሌዎች ስላሳለፉት የቀደሞ ህይዎታቸው እየተጫወቱ ሳለ በእድሜ አነስ የሚለው ሽማግሌ ጥቂት ለሚበልጠው ሽማግሌ "በህይወት ዘመንህ ተመኝተህው የተሳካልህ ነገር አለ ? " ብሎ ይጠይቀዋል

በእድሜ ከፍ ያለው ሽማግሌም ሲመልስ "አዎ አለ በልጂነቴ ጥፋት አጥፍቸ እናቴ ጸጉሬን ስትይዘኝ በጣም ስለሚያመኝ ምነው መላጣ በሆንኩ እል ነበር ይሄው አሁን ተሳክቶልኛል" አለ ይባላል።


thanks wiki