Monday, June 18, 2012

እንጠጋጋለታለን

ዲያስፖራ ያለው አበሻ ትግሬና አማራ የደጋፊና ተቃዋሚ ታቦት ካስቀረጸ በሃላ በጅምላ ገነት እንዳይገባ ተደንግጎበታል ከሰማ ሰነበባብታል። 


ይህን ሰሞን ደግሞ የሚገርም ዜና ሰማሁኝ። አንድ የተከበሩ አበሻ ሞተው መልዓከ ሞት ሕጉን ለማስፈጸም ወደሲኦል ይዛቸው ሲወርድ ሲኦል በሃበሻ ሞልቶ ቦታ ያጣላቸዋል። 


በሰማይ ሕግ መቀመቅ ከሞላ ባለተራው እድለኛ ተብሎ ወደ መንግስተሰማያት ነው የሚገባው ይባላልና ያ የ ሞት መልዓክ እድለኛውን ሰውዩ ይዞ ከ ሲኦል ደጃፍ ወደ መንገደ ገነት ሲያቀና አጥር ላይ ተንጠልጥለው ወሬ የሚያዩ የነበሩ አበሾች አዩና ውስጥ ላለው ሰው ሁሉ ተዳረሰ። 


አንድም ቀን በህይወት እያሉ ተሰማምተው የማያውቁት ሰዎች በኢምንት ተስማሙና በአንድ ድምጽ መልዓኩን ጠሩት


መልዓኩ ባግርሞት "ምነው" አላቸው


አሁንም በ አንድ ድምጽ "ምን እያደረክ ነው ?"አሉት


"እናንተ ጋር ቦታ አጥቼ ገነት እየወሰድኩት ነው" አላቸው


ሳይነጋገሩ ተስማምተው በ አንድ ድም   "አትውሰደው በናትሕ እንጠጋጋለታለን" አሉት ይባላል። ላመናቹን ይህን ቪድዮ ተመልከቱ 











Friday, June 1, 2012

Thinking out of the box የሀበሻ ነገር



መለስ ዜናዊ ሚንስትሮቹን ሰብስቦ ‹‹ሀገራችንን የበለጠ ለማሳደግ እስኪ አዲስ ሀሳብ አምጡ፤ Think out of the box አላቸው››

አንዱ ተነሳና ‹‹ ግብርናን ብናስፋፋ…›› አለ

መለስ ‹‹ ለሱማ ግብርና ሚንስቴር አቋቁመናል፤ Think out of the box አይገባችሁም?›› አለ

ሌላው ተነሳና ‹‹ ኢንደስትሪ ብናስፋፋ…›› አለ

መለስ ‹‹ ኡፎይ! Think out of the box አይገባችሁም፡፡ ለኢንደስቲሪማ ኢንደስትሪ ሚኒስቴር አቋቁመናል›› አለ፡፡

ሚኒስትሮቹ ብዙ ተጨነቁ፡፡

አንዱ ተነሳና ‹‹ Think out of the box ካልከን፤ እስኪ ጀርመንን፤ ጃፓንን፤ ደቡብ ኮርያን፤…እንዲሁም ኢራቅን እናስብ፤ አፍጋኒስታንንም እናስብ፡፡ እኒህ ሀገራት ለምን በለጡን? ለምን አደጉ? ብለን እንጠይቅ፡፡ መልሱ ግልጽ ነው፡፡ አሜሪካንን ለመውጋት ስለሞከሩ፤ አሜሪካ በቦንብ ደብድባ መልሳ ስለገነባቻቸው ነው፡፡ ስለዚህ አሜሪካንን እንውጋ፡፡ ያው አንዱን ከተማ ታጠፋና፤ ሌላውን ሁሉ ትገነባልናለች›› አለ፡፡

መለስ ‹‹ እንዲህ ነው Think out of the box ማለት፡፡ በጣም ጥሩ ነው፡፡ እ…ግን…የሀበሻ ነገር አይታወቅምና ድንገት አሜሪካንን ብናሸንፋትስ›› አለና ጠየቀ፡፡

Tuesday, April 10, 2012

ትንሻን ካርድህን ለምን አትሰጠኝም

ሴትዮዋ ከአገር ቤት ልጃቸው ጋር እዚሕ አማሪካ መጡ። አማሪካ ያዩት ነገር ሁሉ ቢገርማቸውም እንደ ዴቢት ካርድ አድርጎ ያስደነቃቸው ግን አልነበረም። የጉብኝት ቪዛቸው ጌዘው ሲደርስ ወደ አገር ቤት ለመመለስ ሻንጣቸውን ይዘው ከልጃቸው ጋር አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰዋል። 

ልጅ እናቱን የመጨረሻ ሰላምታ ሰጥቶ ሊሰናበታቸው ሲል እናት ያልታሰበ ጥያቄ ልጃቸውን ጠየቁት።

 “ የኔ ልጅ በየጌዜው ገንዘብ በመላክ ከምትቸገር ግድግዳ ወስጥ ስታስገባት ገንዘብ የምትሰጠዋን ትንሻን ካርድህን ለምን አትሰጠኝም”  ብለውት አረፉ።